አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ አጸያፊ ጣዖት ስለ ሠራች ከእቴጌነት ሻራት፤ የሠራችውንም ጣዖት ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በእሳት አቃጠለው።
ዘዳግም 9:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራችሁትንም ጥጃ ምስል፥ ኃጢአት ያደረጋችሁበትንም ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፥ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ያን የኀጢአት ሥራችሁን፣ ያበጃችሁትን ጥጃ ወስጄ በእሳት አቃጠልሁት፤ ከዚያም ሰባብሬ እንደ ትቢያ ዱቄት እስኪሆን ድረስ ፈጭቼ ከተራራው በሚወርደው ጅረት ውስጥ በተንሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያንንም በጥጃ አምሳል አቅልጣችሁ የሠራችሁትን በኃጢአት የተሞላ አጸያፊ ምስል አንሥቼ እሳት ውስጥ ጣልኩት፤ እርሱንም ሰባብሬ እንደ ትቢያ አደቀቅሁት፤ ትቢያውንም ከተራራው በሚወርደው ውሃ ውስጥ ጨመርኩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ አደረጋችሁትም ኀጢአት የጥጃውን ምስል ወሰድሁ፤ በእሳትም አቃጠልሁት፤ አደቀቅሁትም፤ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፤ እንደ ትቢያም ሆነ፤ ትቢያውንም ከተራራው በሚወርድ ወንዝ ጨመርሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፤ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት። |
አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ አጸያፊ ጣዖት ስለ ሠራች ከእቴጌነት ሻራት፤ የሠራችውንም ጣዖት ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በእሳት አቃጠለው።
መሠዊያዎቹንም አፈረሰ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረፁትን ምስሎች አደቀቀ፥ በእስራኤልም አገር ሁሉ የዕጣን መሠዊያዎቹን ሁሉ ቈራረጠ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።
በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን፥ በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ “ከእኔ ራቁ!” ትላቸዋለህ።
የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖቶችዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፤ በግልሙትና ዋጋ ሰብስባቸዋለችና፥ ወደ ግልሙትና ዋጋ ይመለሳሉ።