ዘዳግም 9:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመለከትሁም፥ እነሆ፥ አምላካችሁን ጌታ በድላችሁ ነበር፥ ለእናንተም ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር፤ ጌታ ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርታችሁ እንደ ነበር ተመለከትሁ፤ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስልም ለራሳችሁ አበጃችሁ፤ እግዚአብሔር እናንተን ካዘዛችሁ መንገድ በፍጥነት ወጥታችሁ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰጣችሁ ትእዛዝ ወዲያው ፈቀቅ ብላችሁ፥ ወርቅ አቅልጣችሁ በጥጃ ምስል ጣዖት በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ ማመፃችሁን ተመለከትኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ በአምላካችሁ እግዚአብሔር ፊት እንደ በደላችሁ፥ ለእናንተም ቀልጦ የተሠራ ምስል ሠርታችሁ ልትጠብቁት እግዚአብሔር ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ፈቀቅ እንዳላችሁ ባየሁ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመለከትሁም፤ እነሆ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በድላችሁ ነበር፥ ለእናንተም ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር፤ እግዚአብሔር ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር። |
ከእጃቸው ተቀብሎ በቅርጽ መሥሪያ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃ አደረገው፤ እርሱም፦ “እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” አላቸው።