ዘዳግም 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ! መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ ጌታ እንደ ተናገረ፥ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር፥ እጅግ እንድትበዛ በጥንቃቄ ጠብቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እስራኤል ሆይ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት በምታፈስሰው ምድር መልካም እንዲሆንልህና እጅግ እንድትበዛ፣ ትእዛዙንም ትጠብቅ ዘንድ ጥንቃቄ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነዚህን ሕግጋት አድምጡ! ታዘዙላቸውም! ይህን ብታደርጉ ለቀድሞ አባቶቻችሁ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በማርና በወተት በበለጸገች በዚያች ለም ምድር ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንላችኋል፤ ትበዛላችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ሆይ፥ ስማ፦ ማርና ወተት የምታፈስሰውን ምድር ይሰጥህ ዘንድ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ እጅግ እንድትበዛ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ታደርጋት ዘንድ ጠብቅ።” ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ ያዘዛቸው ሥርዐትና ፍርድ ሁሉ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር እጅግ እንድትበዛ፥ ታደርጋት ዘንድ ጠብቅ። |
በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።
ከግብጽም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ።’
እርሱም፦ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ማየት ፈርቶ ፊቱን ሸፈነ።
ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
የአምላካችንን የጌታን ድምፅ በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፥ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ እኛ ወደ እርሱ የምንልክህን የአምላካችንን የጌታን ድምፅ እንሰማለን።”
ነገር ግን፦ “ድምፄን ስሙ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ” ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።
“እግዚአብሔርም ለአብርሃም የማለለት የተስፋው ዘመን ሲቀርብ፥ ዮሴፍን የማያውቀው ሌላ ንጉሥ በግብጽ ላይ እስኪነሣ ድረስ፥ ሕዝቡ እየተጨመሩ በግብጽ በዙ።
ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ለአባቶቻችን በቃልህ እንደገባኸው መሓላ መሠረት ባርክ።’
የአባቶችህ አምላክ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት፥ ማርና ወተት ወደምታፈሰው ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገር፥ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፍባቸው።
ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ባመጣኋቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
ጠብቁአት አድርጉአትም፥ ይህችን ሥርዓት ሁሉ ሰምተው፦ ‘በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና።