ዘዳግም 5:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን በመጠበቅ እንዲኖሩ፥ ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እነግርሃለሁ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ግን እንዲወርሷት በምሰጣቸው ምድር እንዲጠብቋቸው የምታስተምራቸውን ትእዛዞች፣ ሥርዐቶችና ሕጎች ሁሉ እንድሰጥህ እዚሁ ከእኔ ዘንድ ቈይ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔም ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን ሕግጋቴን፥ ትእዛዞች ሥርዓቶቼን በመጠበቅ እንዲኖሩ ለሕዝቡ አስተምራቸው።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፤ ርስት አድርጌ በምሰጣቸው ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ፍርዴንም ሁሉ እነግርሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፥ ርስት አድርጌ በምሰጣቸውም ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዓቴን ፍርዴንም ሁሉ እነግርሃለሁ። |
ጌታም ሙሴን፦ “ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ እነርሱን እንድታስተምር እኔ የጻፍሁት ሕግና ትእዛዝ ያለበት የድንጋይ ጽላቶች እሰጥሃለሁ” አለው።
“የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ፥ እንድትወርሷት በሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ ሁሉ፥ በጥንቃቄ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።
በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ “ጌታ አምላካችሁ ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ የእናንተ ጦር ሰዎች ሁሉ ታጥቀው በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።
“አሁንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው በሕይወትም እንድትኖሩ፥ የአባቶቻችሁም አምላክ ጌታ ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ የማስተምራችሁን ሥርዓትና ሕግጋት ስሙ።
ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ።