ዘዳግም 5:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ፥ አባትህንና እናትህን አክብር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚእብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ። |
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!
አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፤ ጌታ አምላክህን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፤