ዘዳግም 34:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽ ምድር በፈርዖንና በባርያዎቹ ሁሉ ላይ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን እንዲያደርግ ጌታ የላከው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ልኮት፣ እነዚያን ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆች ሁሉ በግብጽ በፈርዖን፣ በሹማምቱና በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንዲያደርግ የላከውን ያደረገ ማንም ሰው አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ግብጽ ንጉሥና ወደ መኳንንቱ እንዲሁም በመላ ሀገሪቱ ልኮ በእርሱ አማካይነት እንዲፈጸሙ ያደረጋቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራዎች ያሳየ ሌላ ነቢይ ከቶ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅ ምድር በፈርዖንና በሹሞቹ ሁሉ ላይ፥ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብፅ ምድር በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ምልክትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ላከው ያለ፥ |
ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?
ዓይንህ ያየችውን ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ ጌታ አምላክህ ሲያስወጣህ የጸናችውን እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ፥ እንደዚሁ ሁሉ ጌታ አምላክህ አንተ በምትፈራቸው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደርጋል።