ዘዳግም 33:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በሞገስ ጠግቧል፥ የጌታንም በረከት ተሞልቶአል፥ ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በእግዚአብሔር ሞገስ ረክቷል፤ በበረከቱም ተሞልቷል፤ ባሕሩንና የደቡብን ምድር ይወርሳል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ንፍታሌም ነገድ እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በጌታ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነው፤ በእግዚአብሔር በረከትም ተሞልቶአል፤ ግዛቱም እስከ ባሕሩና ወደ ደቡብ የተዘረጋ ነው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም ከበጎ ነገር ጠግቦአል፤ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕርንና ሊባን ይወርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ 2 ንፍታሌም በሞገስ ጠግቦአል፥ 2 የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ 2 ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል። |