ወደ እርሱም ቀረበ፥ ሳመውም፥ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፥ ባረከውም፥ እንዲህም አለ፦ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፥
ዘዳግም 33:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፥ “ምድሩ ከጌታ ዘንድ የተባረከ ይሁን፤ ከሰማያት በሚዘንበው የላቀ ስጦታ፥ ከታችም ከጥልቀት ከሚገኘው ውሃ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦ “እግዚአብሔር ምድሩን ይባርክ፤ ድንቅ የሆነውን ጠል ከላይ ከሰማይ በማውረድ፣ ከታች የተንጣለለውን ጥልቅ ውሃ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ዮሴፍም ነገድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከላይ በሰማይ በሚዘንብ ዝናብ፥ ከታችም ከጥልቀት በሚገኘው ውሃ፥ ምድራቸውን ይባርክ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፦ ምድሩ ከእግዚአብሔር በረከት፥ ከሰማይ ዝናምና ጠል፥ ከታችም ከጥልቁ ምንጭ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፥ 2 ምድሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረከ ይሁን፤ 2 በሰማያት ገናንነት በጠል፥ 2 በታችኛውም ቀላይ፥ |
ወደ እርሱም ቀረበ፥ ሳመውም፥ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፥ ባረከውም፥ እንዲህም አለ፦ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፥
አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፥ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።
በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋ መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ የያዕቆብ ትሩፍም በአሕዛብና በብዙ ሕዝቦች መካከል እንዲሁ ይሆናል።
ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፥ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠልአቸውን ይሰጣሉ፤ ለዚህም ቀሪ ሕዝብ ይህን ነገር ርስት አድርጌ እሰጣለሁ።
“ከዮሴፍ ልጆች፥ የኤፍሬም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬ እንደ ጠል ይንጠባጠብ፤ በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ በሣርም ላይ እንደ ካፊያ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ዝናብ፥