ዘዳግም 32:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፥ አባትህን ጠይቅ፥ እርሱም ያስታውቅሃል፥ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ እነርሱም ይነግሩሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤ አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውን አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ እርሱም ይነግርሃል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ እነርሱም ይተርኩልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዱሮውን ዘመን አስብ፤ የልጅ ልጅንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ይነግርህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፤ ይተርኩልህማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዱሮውን ዘመን አስብ፥ 2 የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ 2 አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ 2 ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። 2 |
እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ ጌታ በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብጽ አወጣን፤
እርሱም የቀደመውን ዘመን እንዲህ ብሎ አሰበ፦ የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለው? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለው?
“እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረው ጊዜ ጀምሮ፥ ከሰማይ ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቅ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደሆነ ከአንተ በፊት የነበረውን የቀደመውን ዘመን ጠይቅ።
ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።
ጌዴዎን መልሶ፥ “ጌታዬ ሆይ ጌታ ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ሁሉ እንዴት ሊደርስብን ቻለ? ‘ጌታ ከግብጽ ምድር አውጥቶናል’ በማለት አባቶቻችን የነገሩን ታምራት የት አለ? አሁን ግን ጌታ ትቶናል፤ በምድያማውያንም እጅ አሳልፎ ሰጥቶናል” አለው።