Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 13:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እንዲህም ይሆናል በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፦ ይህ ምንድነው? ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ ጌታ በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብጽ አወጣን፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ እንዲህ በለው፤ ‘ከባርነት ምድር ከግብጽ እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ አወጣን፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህን ሥርዓት ትርጒም ቢጠይቁህ፥ እንዲህ በማለት ታስረዳቸዋለህ፦ ‘በባርነት ከተገዛንበት ከግብጽ ምድር እግዚአብሔር በታላቅ ኀይል አወጣን፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምን​ድን ነው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ርቱ እጅ ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እንዲህም ይሆናል፤ በሚመጣው ጊዜ ልጅህ፥ ‘ይህ ምንድር ነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር አወጣን፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 13:14
29 Referencias Cruzadas  

ይህም በመካከላችሁ ምልክት ይሆናል፤ ልጆቻችሁም በሚመጣው ዘመን፦ ‘ለእናንተ እነዚህ ድንጋዮች የሚሰጡት ትርጒም ምንድነው?’ ብለው ሲጠይቁአችሁ፥


ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።


ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥ ኃይልህንም ያወራሉ።


ይልቁንም ይህን ያደረግነው ከልባችን ፍርሃት የተነሣ ሲሆን እንዲህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ ‘ከእስራኤል አምላክ ከጌታ ጋር ምን ነገር አላችሁ?


በእጅህ እንደ ምልክት በዐይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ፥ የጌታ ሕግ በአፍህ እንዲሆን፥ ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶሃልና።


ይህም በልጅህና በልጅ ልጅህ ጆሮ እንድትነግርና ግብፃውያንን እንዴት እንዳሞኘኋቸው፥ በመካከላቸው ያስቀመጥኩት ምልክቶቼም ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።”


ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደ ፊት ጻድቅነቴ ይመሰክርልኛል፥ ከፍየሎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ የሌለበት ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቆጠርብኝ።”


የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መርጦ በግብጽ አገር በእንግድነት ሳሉ ሕዝቡን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ከፍ ባለችውም ክንዱ ከዚያ አወጣቸው።


ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ጌታ ነኝ፥ ከግብፃውያን ጭቆና አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታችሁም አላቅቃችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድ በታላቅ የፍርድ ሥራም አድናችኋለሁ፤


በዚያም ቀን፦ “ከግብጽ በወጣሁ ጊዜ ጌታ ስላደረገልኝ ነው” ስትል ለልጅህ ትነግረዋለህ።


ከልጆቻቸው አንሰውረውም፥ ለሚመጣውም ትውልድ የጌታን ምስጋናና ኃይሉን ያደረገውንም ተኣምራት እንናገራለን።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሁን ፈርዖንን ምን እንደማደርገው ታያለህ በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋል፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋል።”


ለእኔ ሕዝብ አድርጌ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብጽ ጭቆና ያወጣኋችሁ ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


እንዲህም ሆነ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ በዚህ ቀን የጌታ ሠራዊት ሁሉ ከግብጽ ምድር ወጡ።


“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


“ ‘ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህ አስታውስ፥ ጌታ እግዚአብሔር በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፥ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ትጠብቅ ዘንድ አዘዘህ።


በዚያን ጊዜ ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ጌታ እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።


እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባቸውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ ጌታ አምላካችን ነውና።


ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ተው፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም፤ ጌታንም አስቈጡት፤


ጌታ አንድ ነቢይ ላከላቸው፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል ከባርነት ቤት ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ነኝ።


ተአምራቱንም የተናገረውንም ፍርድ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፤ እናንተ


እነዚህም በታላቁ ኃይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባርያዎችህና ሕዝብህ ናቸው።


እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios