ዘዳግም 32:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተሰበሰበ ሁሉ፥ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፥ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተሰበሰበ ሁሉ፣ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ ሞቶ ወደ ወገኖቹ እንደ ተቀላቀለ አንተም በዚሁ በነቦ ተራራ ላይ ሞተህ ከወገኖችህ ጋር ትቀላቀላለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም እንደ ተጨመረ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተጨመር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምህም አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ ወደ ወገኖቹም እንደ ተከማቸ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፥ ወደ ወገኖችህም ተከማች፤ |
ካህኑም አሮን በጌታ ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ።
ጌታ ሙሴን፥ “እነሆ የምትሞትበት ቀን ቀርቧል፤ ትእዛዝ እንድሰጠው ኢያሱን ጥራውና ወደ መገናኛው ድንኳን ቅረቡ።” ሙሴና ኢያሱም ሄዱ፤ ወደ መገናኛው ድንኳንም ቀረቡ።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።