አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ፤ እጃችሁንም ለጌታ ስጡ፥ ለዘለዓለም ወደተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፥ ጽኑ ቁጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን ጌታን አገልግሉ።
ዘዳግም 31:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፥ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በጌታ ላይ ዐምፃችኋል፥ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቱን ያህል ዐመፀኞችና ዐንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ ዐውቃለሁና። እኔ በሕይወት ከእናንተ ጋራ እያለሁ በእግዚአብሔር ላይ ካመፃችሁ፣ ከሞትሁ በኋላማ የቱን ያህል ልታምፁ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ምን ያኽል ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆኑ ዐውቃለሁ፤ በእኔ ሕይወት ዘመን ከእነርሱ ጋር ሳለሁ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፁ ናቸው፤ ከሞትሁ በኋላማ ከዚህ ይበልጥ ያምፃሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ዐመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፤ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል፤ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፤ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል፤ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል? |
አባቶቻችሁም እንደ ነበሩ አንገተ ደንዳና አትሁኑ፤ እጃችሁንም ለጌታ ስጡ፥ ለዘለዓለም ወደተቀደሰው ወደ መቅደሱም ግቡ፥ ጽኑ ቁጣውም ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን ጌታን አገልግሉ።
ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፥ ነገር ግን ታበዩ፥ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርድህን ተላለፉ፥ ትከሻቸውንም ሰጡ፥ አንገታቸውን አደነደኑ፥ አልሰሙምም።
ልጆች ግን ዐመፁብኝ፥ ሰው ቢያደርገው ኖሮ በሕይወት የሚኖርባትን ፍርዴን ጠብቀው አላደረጓትም በሥርዓቴም አልሄዱም፥ ሰንበታቴንም አረከሱ፤ በዚህም ጊዜ፦ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ ቁጣዬንም በምድረ በዳ እፈጽምባቸዋለሁ አልሁ።
“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፤ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።
“በእናንተ ላይ ምስክር ሆኖ በዚያ ይኖር ዘንድ በጌታ በእግዚአብሔር የኪዳን ታቦት አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በእናንተ ላይ ምስክር ሆኖ በዚያ ይኖራል፤
“ጌታ አምላክህ ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ፥ በልብህ፥ ‘እንድንወርሳት ወደዚች ምድር ጌታ ያስገባኝ በጽድቄ ምክንያት ነው’ አትበል፤ ጌታ እነዚህን ሕዝቦች ከፊትህ ያስወጣቸው ስለ ኃጢአታቸው ነው።