La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ጌታ አምላካችን ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዖግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፥ እኛም አንድ ሰው እንኳ ሳናስቀርለት አጠፋነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ አምላካችን እግዚአብሔር የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመላው ሰራዊቱ ጋራ ሁሉ እንደዚሁ በእጃችን ላይ ጣላቸው፤ እኛም አንድ እንኳ በሕይወት ሳናስቀር አጠፋናቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካችን የባሳንን ንጉሥ ዖግንና ሕዝቡን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም ከእነርሱ አንድ እንኳ ሳናስቀር ሁሉንም አጠፋን።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን፤ እኛም አጠ​ፋ​ነው፤ አንድ ሰው እን​ኳን ለዘር አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምላካችን እግዚአብሔርም ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዐግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም መታነው፤ አንድ ሰው እንኳ አምልጦ አልቀረለትም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 3:3
9 Referencias Cruzadas  

የባሳንን ንጉሥ ዐግን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


ለእርሱም አንድ ሰው በሕይወት እንዳይተርፍ አድርገው እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ ገደሉ፤ ምድሩንም ወረሱ።


ቂጣ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።


ጌታም፦ ‘እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁና አትፍራው፥ በሐሴቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግህ በእርሱም ታደርግበታለህ’ አለኝ።”


ያን ጊዜም ከተሞቹ ሁሉ ያዝን፥ የአርጎብን ግዛቶች ሁሉ፥ ከሥልሳ ከተሞች ጋር፥ በባሳን ያለውን የዖግን መንግሥት፥ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም።


እነርሱም የእርሱን ምድርና እንዲሁም በዮርዳኖስ ምሥራቅ የምትገኘውን ባሳንን ይገዛ የነበረውን የሌላውን አሞራዊ ንጉሥ የዖግን ምድር ወረሱ።


በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፤ እርሱም ብቻ ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ ድል አድርጎ አስወጣቸው።


ግዛታቸውም ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥