ዘዳግም 29:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ፥ በሰፈራችሁም ያለ እንጨትህን የሚቆርጥ ውኃህንም የሚቀዳ መጻተኛ አብረውህ ቆመዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ ዕንጨትህን እየፈለጡ፣ ውሃህንም እየቀዱ በሰፈርህ የሚኖሩ መጻተኞችም ዐብረውህ ቆመዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቶቻችሁም፥ ልጆቻችሁም ከእንጨት ለቃሚያችሁ እስከ ውኃ ቀጃችሁ በሰፈራችሁ ያለ መጻተኛ፤ |
ከወንድሞቻቸውና ከመኳንንቶቻቸው ጋር በመሆን በእግዚአብሔር ባርያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ለመሄድ፥ የጌታ አምላካችንን ትእዛዞቹን ሁሉ፥ ፍርዶቹንና ሥርዓቶቹን ለመጠበቅና ለማድረግ ወደ እርግማንና መሐላ ገቡ።
በእነርሱም መካከል የነበረው የተለያየ ሕዝብ እጅግ ጐመጀ፤ የእስራኤልም ልጆች ዳግመኛ ዘወር በለው አለቀሱ እንዲህም አሉ፦ “የምንበላውን ሥጋ ማን ይሰጠናል?
“እናንተ ሁላችሁ መሪዎቻችሁና አለቆቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁና ሹሞቻችሁ እንዲሁም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዛሬ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤
ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላካችሁ ሰንበት ነው፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም አገልጋይህም፥ አገልጋይትህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ ወይም በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ፥ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፥ አንተ እንደምታርፍ ሁሉ አገልጋይህና አገልጋይትህ እንዲያርፉ።
በዚህም መታደስ ግሪካዊና አይሁዳዊ፥ የተገረዘና ያልተገረዘ፥ አረማዊና እስኩቴስ፥ ባርያና ነጻ ሰው የሚባል ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።
ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ በሴቶቹም በሕፃናቱም በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል እንኳ ሳያስቀር ሁሉን አነበበ።