ዘዳግም 28:67 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፥ ሲነጋ፥ ‘ይመሽ ይሆን?’ ሲመሽ ደግሞ፥ ‘ይነጋ ይሆን?’ ትላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፣ ሲነጋ፣ “ምነው አሁን በመሸ!” ሲመሽ ደግሞ፣ “ምነው አሁን በነጋ!” ትላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልብህን በሚሞላው ፍርሀትና በዐይንህ በምታየው አስደንጋጭ ትርኢት ምክንያት፥ ሲነጋ መቼ በመሸልኝ፥ ሲመሽም መቼ በነጋልኝ ትላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈራህበት ከልብህ ፍርሀት የተነሣ፥ በዐይንህም ካየኸው የተነሣ፥ ሲነጋ እንዴት ይመሽ ይሆን? ትላለህ፤ ሲመሽም እንዴት ይነጋ ይሆን? ትላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ስለ ፈራህበት ስለ ልብህ ፍርሃት፥ በዓይንህም ስለምታየው አስተያየት፥ ማለዳ፦ መቼ ይመሻል? ትላለህ፤ ማታም፦ መቼ ይነጋል? ትላለህ። |
ከእንግዲህ ወዲያ አትመለስባትም ባልሁህ መንገድም ጌታ በመርከብ ወደ ግብጽ ይመልስሃል። እዚያም ወንዶችና ሴቶች ባሮች እንድትሆኗቸው ለጠላቶቻችሁ ራሳችሁን ትሸጣላችሁ፥ የሚገዛችሁ ግን አይገኝም።”