Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 28:66 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

66 ቀንም ሆነ ሌሊት በፍርሀት እንደ ተዋጥህ፥ ሕይወትህ ዋስትና ሳታገኝ፥ ዘወትር በሥጋት ትኖራለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

66 ቀንም ሆነ ሌሊት በፍርሀት እንደ ተዋጥህ፣ ሕይወትህ ዋስትና ሳታገኝ፣ ዘወትር በሥጋት ትኖራለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

66 ሕይወትህ ዘወትር በጭንቀት ላይ ይሆናል፤ የመኖር ዋስትናህም የተረጋገጠ ባለመሆኑ ቀንና ሌሊት በፍርሃት ትዋጣለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

66 ሕይ​ወ​ትህ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት የተ​ሰ​ቀ​ለች ትሆ​ና​ለች፤ ሌሊ​ትና ቀንም ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለህ፤ በሕ​ይ​ወ​ት​ህም አት​ታ​መ​ንም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

66 ነፍስህም ታመነታለች፤ ሌሊትና ቀንም ትፈራለህ፥ በሕይወትህም አትታመንም፤

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 28:66
5 Referencias Cruzadas  

ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፥ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ።


በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። በዚያም ጌታ የሚርድ ልብ፥ ፈዛዛ ዐይኖች፥ ደካማም ነፍስ ይሰጥሃል።


ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፥ ሲነጋ፥ ‘ይመሽ ይሆን?’ ሲመሽ ደግሞ፥ ‘ይነጋ ይሆን?’ ትላለህ።


ነገር ግን የሚያስፈራ የፍርድና ተቃዋሚዎችንም ለመብላት የሚጠብቅ የእሳት ግለት አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos