Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 28:68 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

68 ከእንግዲህ ወዲያ አትመለስባትም ባልሁህ መንገድም ጌታ በመርከብ ወደ ግብጽ ይመልስሃል። እዚያም ወንዶችና ሴቶች ባሮች እንድትሆኗቸው ለጠላቶቻችሁ ራሳችሁን ትሸጣላችሁ፥ የሚገዛችሁ ግን አይገኝም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

68 ዳግመኛ አትመለስባትም ባልሁህ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብጽ ይመልስሃል። እዚያም ወንዶችና ሴቶች ባሮች እንድትሆኗቸው ለጠላቶቻችሁ ለመሸጥ ራሳችሁን ታቀርባላችሁ፤ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

68 እግዚአብሔር ‘ዳግመኛ ተመልሰህ ወደዚያ አትሄድም’ ብሎ የተናገረ ቢሆንም እንኳ በመርከብ ተሳፍረህ ወደ ግብጽ እንድትመለስ ያደርጋል፤ በዚያም ራስህን ለጠላቶችህ ባሪያ አድርገህ መሸጥ ትፈልጋለህ፤ ነገር ግን ባሪያ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልግህ እንኳ አታገኝም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

68 ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተመ​ል​ሰህ አታ​ያ​ትም ባል​ሁህ መን​ገ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ር​ከብ ወደ ግብፅ ይመ​ል​ስ​ሃል፤ በዚ​ያም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የሚ​ራ​ራ​ላ​ች​ሁም አይ​ኖ​ርም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

68 ከእንግዲህ ወዲህ ተመልሰህ አታያትም ባልሁህ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልስሃል፤ በዚያም ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ትሆኑአቸው ዘንድ ለጠላቶቻችሁ ራሳችሁን ትሸጣላችሁ፤ የሚገዛችሁም አይገኝም።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 28:68
14 Referencias Cruzadas  

ወደ ግብጽም ለመግባት በዚያም ለመቀመጥ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ትሩፍ እወስዳለሁ፥ ሁሉም ይጠፋሉ፥ በግብጽም ምድር ይወድቃሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለመሣቀቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።


በጌታ ምድር ላይ አይቀመጡም፤ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኩስን ነገር ይበላሉ።


የጌታንም ድምፅ አልሰሙምና ወደ ግብጽ ምድር ገቡ፥ እስከ ጣፍናስ ድረስ መጡ።


የተመረጠውን መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፤ ጌታ ግን በእነርሱ ደስ አይሰኝም፤ በደላቸውን አሁን ያስታውሳል፥ ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።


በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉ ይሰደዳሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።


ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና።


እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ “ለአሕዛብ የተሸጡትን አይሁድ ወንድሞቻችንን በተቻለን መጠን ተቤዠን፥ እናንተ ደግሞ ወንድሞቻችሁን ትሸጣላችሁ? እነርሱስ ለእኛ ይሸጣሉን? እነርሱም ዝም አሉ፥ የሚመልሱትንም ቃል አጡ።


“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።


ያ ባርያ ግን ‘ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል’ ብሎ በልቡ ቢያስብ ሎሌዎችንና ገረዶችንም ይመታ ይበላም ይጠጣም ይሰክርም ዘንድ ቢጀምር፥


ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፥ ሲነጋ፥ ‘ይመሽ ይሆን?’ ሲመሽ ደግሞ፥ ‘ይነጋ ይሆን?’ ትላለህ።


ጌታ በኮሬብ ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞዓብ ምድር ከእስራኤላውያን ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው የኪዳኑ ቃሎች የሚከተሉት ናቸው፦


እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ምንም እንኳን ቅርብ ቢሆን በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ “ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብጽም እንዳይመለስ” ብሏልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios