ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።
ዘዳግም 28:56 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከልህ ተለሳልሳና ተቀማጥላ የምትኖር፥ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ እግሮችዋ ዐፈር ነክቶት የማያውቁ ሴት ዐቅፋው ለምትተኛው ባሏና በገዛ ወንድ ወይም ሴት ልጆችዋ ላይ ትከፋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከልህ ተለሳልሳና ተቀማጥላ የምትኖር፣ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ፣ እግሯን ዐፈር ነክቶት የማያውቅ ሴት፣ የምትወድደውን ባሏን፣ የገዛ ወንድ ወይም ሴት ልጆቿን ትንቃለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመለሳለስና በቅምጥልነት በመካከልህ የምትኖር በትውልድዋ የምትመካና ከመለስለስዋ ብዛት እግሮችዋ መሬት ረግጠው የማያውቁ ዐቅፋው ከምትተኛው ባልዋና ከልጆችዋ ትሰስታለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንተ ዘንድ የተለሳለሰችና የተቀማጠለች፥ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ የእግር ጫማዋን በምድር ላይ ያላደረገችው ሴት፥ አቅፋ በተኛችው ባልዋ፥ በወንድና በሴት ልጅዋም ትቀናለች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንተ ዘንድ ያለችው የተለሳለሰችና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ትኖር የነበረችው፥ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ የእግር ጫማዋን በምድር ላይ ያላደረገችው ሴት፥ አቅፋ በተኛችው ባልዋ፥ |
ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ታህል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ምክንያቱም ከተሞችህ ሁሉ ጠላቶችህ ከበው ከሚያደርሱብህ ሥቃይ የተነሣ ከዚህ በቀር የተረፈው የለም።