Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 28:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 በመካከልህ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ፥ አቅፋውም ለምትተኛ ለሚስቱ፥ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይሳሳም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 ሌላው ይቅርና በመካከልህ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ ወይም ለሚወድዳት ሚስቱ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይራራላቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 በመካከላችሁ በመለሳለስና በቅምጥልነት በትውልዱም በመመካት የሚኖረው ሰው እንኳ ለወንድሙ፥ ዐቅፋው ለምትተኛው ሚስቱና ከጥፋት ለተረፉት ልጆቹ ከዚያ ምግብ ለመስጠት ይሰስታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 በአ​ንተ ዘንድ የተ​ደ​ላ​ደ​ለና የተ​ቀ​ማ​ጠለ ሰው በወ​ን​ድሙ፥ አብ​ራ​ውም በም​ት​ተኛ በሚ​ስቱ፥ በቀ​ሩ​ትም ልጆቹ ይቀ​ናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 በአንተ ዘንድ የተለሳለሰና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ይኖር የነበረ ሰው በወንድሙ፥ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ፥ በቀሩትም ልጆች ይቀናል፤

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 28:54
14 Referencias Cruzadas  

ድኻው ግን ከገዛት ከአንዲት ጠቦት በግ በስተቀር ሌላ አልነበረውም። እየተንከባከበ አብራውም ከልጆቹ ጋር አደገች፤ አብራው ትበላ፤ ከጽዋውም ትጠጣ እንዲሁም በዕቅፉ ትተኛ ነበር፤ ልክ እንደገዛ ልጁ ነበረች።


አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ጌታም ለሚፈሩት ይራራል፥


የንፉግን ሰው እንጀራ አትብላ፥ ጣፋጩ መብልም አይመርህ፥


ምቀኛ ሰው ሀብታም ለመሆን ይጣደፋል ችጋርም እንደሚመጣበት አያውቅም።


በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ የተወለደው ሕጻን ልጇን ትረሳለች? ርህራሄ አልባስ እስክመሆን ትደርሳለች? አዎን፥ እርሷ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም።


በጓደኛ አትታመኑ፥ በወዳጅም አትተማመኑ፤ የአፍህን ደጅ በጉያህ ከምትተኛው ጠብቅ።


ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ።


የራሴ በሆነ ነገር ላይ የወደድሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንኩ ትመቀኛለህን?


“የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥


‘ዕዳ የሚሠረዝበት ሰባተኛው ዓመት ተቃርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ አድሮብህ፥ በችግረኛ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፥ እርሱም በአንተ ላይ ወደ ጌታ ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!


“ጠላቶችህ ከበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፥ ከሥቃይ የተነሣ፥ ጌታ እግዚአብሔር የሰጠህን፥ የሆድህ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።


ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ታህል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ምክንያቱም ከተሞችህ ሁሉ ጠላቶችህ ከበው ከሚያደርሱብህ ሥቃይ የተነሣ ከዚህ በቀር የተረፈው የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos