ዘዳግም 28:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትተማመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪማረኩ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከባል፤ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትታመንባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገርህ ያሉትን ከተሞችህን ሁሉ ይከብባል፤ አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወርራቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚገኙትን መኖሪያ ከተሞችህን ሁሉ ይከባሉ፤ አንተ የምትተማመንባቸውን ከፍተኞች የሆኑ ቅጽሮች ያሉአቸውን ምሽጎችህን ሁሉ ይደመስሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሀገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ፥ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ሁሉ ያጠፋሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ፥ በደጆች ሁሉ ያስጨንቅሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ደጆች ሁሉ ከብበው ያስጭንቁሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ በደጆች ሁሉ ከብበው ያስጨንቁሃል። |
ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።
የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ።
እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የሚያንገዳግድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ ደግሞም ይሁዳ እንደተከበበች ኢየሩሳሌም እንዲሁ ትከበባለች።
አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እንዲነሱ እሰበስባቸዋለሁ፤ ከተማይቱም ትያዛለች፥ ቤቶችም ይበዘበዛሉ፥ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማይቱም እኩሌታ ለምርኮ ይጋዛል፥ የቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዋ አይፈናቃልም።
እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬና የምድርህን ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ የእህል፥ የወይን ወይም የዘይት፥ የከብትህን ጥጃ ወይም የበግና ፍየል መንጋህን አይተውልህም።