“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር ቢመጣ፥ በውርጭ፥ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ ቢትወረር፥ የሕዝብህም ጠላት የአገሩን ቀበሌዎች ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
ዘዳግም 28:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በእርሻ ላይ ብዙ ዘር ትዘራለህ፤ አንበጣ ስለሚበላው የምትሰበስበው ጥቂት ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዕርሻ ላይ ብዙ ዘር ትዘራለህ፤ አንበጣ ስለሚበላው ግን፣ የምትሰበስበው ጥቂት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእህልህን ሰብል አንበጣ ስለሚበላው ብዙ እህል ዘርተህ ጥቂት መከር ብቻ ትሰበስባለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ዘርም ወደ እርሻ ታወጣለህ፤ አንበጣም ይበላዋልና ጥቂት ትሰበስባለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጅግ ዘር ወደ እርሻ ታወጣለህ፤ አንበጣም ይበላዋልና ጥቂት ትሰበስባለህ። |
“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር ቢመጣ፥ በውርጭ፥ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ ቢትወረር፥ የሕዝብህም ጠላት የአገሩን ቀበሌዎች ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።
እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፥ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፥ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም።
“በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፤ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።
ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልሰከራችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ለማስቀመጥ ደመወዙን ተቀበለ።
እናንተ ብዙ ነገርን ፈልጋችሁ፥ እነሆ ጥቂት ሆነ፤ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። በምን ምክንያት? ይላል የሠራዊት ጌታ። ምክንያቱም እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ስለፈረሰ ነው።
እነሆ፥ ዘራችሁን እገሥጻለሁ፥ በፊታችሁ ላይ ፈርስን እበትናለሁ፥ ይህም ፈርስ ለበዓላችሁ መሥዋዕት ካመጣችኋቸው ነው፤ እናንተንም ከእርሱ ጋር ያነሳችኋል።