“ሕዝብህ እስራኤል አንተን ስለ በደሉ በጠላቶቻቸው ፊት ድል ቢመቱ፥ ነገር ግን ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ በዚህም ቤት ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥
ዘዳግም 28:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ በሚደርስብህም ነገር ለምድር መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በጠላቶችህ ፊት እንድትሸነፍ ያደርግሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሸሻለህ፤ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀቂያ ትሆናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፤ በሰባት መንገድም ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ የተበተንህ ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፥ በሰባት መንገድ ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ ለምድርም መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ። |
“ሕዝብህ እስራኤል አንተን ስለ በደሉ በጠላቶቻቸው ፊት ድል ቢመቱ፥ ነገር ግን ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ስምህንም ቢያከብሩ፥ በዚህም ቤት ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥
የእስራኤል ልጆች ከወንድሞቻቸው ሁለት መቶ ሺህ ሴቶችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ማረኩ፥ ብዙም ምርኮ ከእነርሱ ወስደው ወደ ሰማርያ አገቡ።
“ሕዝብህም እስራኤል በአንተ ላይ ኃጢአት ስለ ሠሩ በጠላት ፊት ድል ተመትተው ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ስምህንም ቢጠሩ፥ በዚህም ቤት በፊትህ ቢጸልዩና ቢለምኑህ፥
ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፥ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፥ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ።
በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።
በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆናሉ፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤና ለክፉ ነገር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
በሰይፍም በራብም በቸነፈርም አሳዳድዳቸዋለሁ፤ ባሳደድኋቸውም አሕዛብ ሁሉ መካከል ለመረገሚያና ለመሣቀቂያ ለማፍዋጫም ለመሰደቢያም ይሆናሉ፤ በምድር መንግሥታትም ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
“ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምድር መንግሥታትም ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።
“ጌታ በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ።
ፍልስጥኤማውያንም ተዋጉ፤ እስራኤላውያንም ስለ ተሸነፉ እያንዳንዱ ወደየድንኳኑ ሸሸ። ታላቅ እልቂትም ሆነ፤ ከእስራኤልም ሠላሳ ሺህ እግረኛ ወታድሮች ወደቁ።