ዘዳግም 25:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እህል በምታበራይበት ጊዜ የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እህልህን በምታበራይ ጊዜ በሬዉን አፉን አትሰረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እህል የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። |
ኤፍሬም ማበራየት የምትወድ የተገራች ጊደር ነበር፥ እኔም በውብ አንገትዋ ላይ አልጫንኩባትም፤ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፥ ይሁዳም ያርሳል፥ ያዕቆብም ለራሱ አፈሩን ያለሰልሳል።