አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።
ዘዳግም 22:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ፥ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ በቤትህ ላይ የደም በደል እንዳታመጣ፥ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጅለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ፣ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ በቤትህ ላይ የደም በደል እንዳታመጣ፣ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጅለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ በጣራው ክፈፍ ዙሪያ መከታ አድርግለት፤ አለበለዚያ አንድ ሰው ከጣራው ላይ ቢወድቅ ለደሙ ተጠያቂ ትሆናለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አዲስ ቤት በሠራህ ጊዜ ማንም ከእርሱ ወድቆ በቤትህ ግድያ እንዳታደርግ ለሰገነትህ መከታ አድርግለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዲስ ቤት በሠራህ ጊዜ ማንም ከእርሱ ወድቆ ደሙን በቤትህ ላይ እንዳታመጣ በጣራው ዙሪያ መከታ አድርግለት። |
አንድ ቀን ማታ፥ ዳዊት ከአልጋው ተነሥቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ ከሰገነቱ ላይ እንዳለም፥ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ ውብ ነበረች።
የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፥ እነዚያ በሰገነቶቻቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ ያጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቁርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ፥ እንደ ቶፌት ስፍራ የረከሱ ይሆናሉ።’ ”
እኔ ኃጢአተኛውን፦ ሞትን ትሞታለህ ባልሁት ጊዜ፥ ካላስጠነቀቅኸው፥ ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን አስጠንቅቀህ ካልነገርኸው፥ ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
ጻድቁ ደግሞ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአት ከሠራ፥ እኔም በፊቱ ዕንቅፋትን አደርጋለሁ፥ እርሱም ይሞታል፤ አንተም አላስጠነቀቅኸውምና በኃጢአቱ ይሞታል፥ የጽድቁም ሥራ አይታሰብለትም፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
እንግዲህ ከዚህ በኋላ አንዳችን በአንዳችን ላይ አንፍረድ፤ ነገር ግን ከመፍረድ ይልቅ ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይወስን።
እንዲህም ያለው እውቀት የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ እንድትወድዱ ስለሚረዳችሁ ነው፤ በዚህም ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ንጹሖችና ያለ ነቀፋ በመሆን