ዘዳግም 21:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሷ ደስተኛ ባትሆን፥ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጣት፤ ውርደት ላይ ጥለሃታልና አትሽጣት ወይም እንደ ባርያ አትቁጠራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሷ ደስተኛ ባትሆን፣ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጣት፤ ውርደት ላይ ጥለሃታልና ልትሸጣት ወይም እንደ ባሪያ ልትቈጥራት አይገባህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኋላ ግን የማትፈልጋት ከሆንህ ነጻ ልትለቃት ትችላለህ፤ ከአንተ ጋር የጋብቻ ግንኙነት እንድትፈጽም ያስገደድሃት ስለ ሆንክ ባሪያ አድርገህ ልትሸጣት አይገባም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ በእርስዋ ደስ ባይልህ አርነት አውጥተህ ትለቅቃታለህ፤ በዋጋ ግን አትሸጣትም፤ አግብተሃታልና እንደባሪያ አትቍጠራት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ በእርስዋ ደስ ባይልህ አርነት አውጥተህ ወደ ወደደችው ትሰድዳታለህ፤ በዋጋ ግን አትሸጣትም፤ እፍረት አድርገህባታልና እንደ ባሪያ አትቈጥራትም። |
“አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፤ አንደኛዋን የሚወዳት፥ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፥ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኩር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥
በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል በማስከፈል ለብላቴናይቱም አባት ይስጡት፥ እርሷም ሚስቱ ሆና ትኑር፥ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።”
ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፥ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዬውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፥ በዚህም ዓይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።
እነሆ ድንግል የሆነች ልጄና የሰውየው ቊባት አሉ፤ እነርሱን አሁኑኑ ላውጣላችሁና አስነውሯቸው፤ ያሻችሁንም አድርጉባቸው፤ በዚህ ሰው ላይ ግን እንዲህ ያለውን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙበት።”