ዘዳግም 20:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ፥ አስቀድመህ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ፣ አስቀድመህ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በአንዲት ከተማ ላይ አደጋ ለመጣል በምትዘምትበት ጊዜ በመጀመሪያ እንዲገብሩ የሰላም ድርድር ጠይቅ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለመዋጋት ወደ አንዲት ከተማ በደረስህ ጊዜ አስቀድመህ በሰላም ቃል ጥራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመዋጋት ወደ አንዲት ከተማ በደረስህ ጊዜ አስቀድመህ በዕርቅ ቃል ጥራቸው። |
ሠረገላውንም ከኤፍሬም፥ ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ፤ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።