ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም ረጅም ጊዜ ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።
ዘዳግም 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘በዚህ ተራራማ አገር ለረጅም ጊዜ ተንከራታችኋልና ይብቃችሁ፥ ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሂዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚህ በኰረብታማ አገር ዙሪያ እስኪበቃችሁ ተንከራታችኋል፤ አሁን ግን ወደ ሰሜን ተመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘በእነዚህ ኮረብታማ አገሮች የተንከራተታችሁበት ጊዜው ረጅም ነው፤ አሁን ግን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ሂዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል፤ ተመልሳችሁ ወደ መስዕ ሂዱ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ተራራ መዞር ይበቃችኋል፤ ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሂዱ። |
ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም ረጅም ጊዜ ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።
የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ ጌታ እንደ ማለባቸው የጦረኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።
ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር ላይ በተቀመጡት በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች አገር ታልፋላችሁ፥ እነርሱም ይፈሩአችኋል፤ እንግዲህ እጅግ ተጠንቀቁ።
“ጌታ አምላክህ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፥ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፥ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም።