ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ሙሉ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።
ዘዳግም 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁንም፥ ‘ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ አለን። የዘሬድንም ፈፋ ተሻገርን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር “አሁኑኑ ተነሡና የዘሬድን ደረቅ ወንዝ ተሻገሩ” አለን፤ እኛም ወንዙን ተሻገርን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር በነገረን መሠረት የዘሬድን ወንዝ ተሻገርን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ‘ተነሡና ተጓዙ፤ የዛሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ የዛሬድንም ፈፋ ተሻገርን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፦ ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ አለ። |
ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ሙሉ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።
ከዚያም ተጉዘው ከአሞራውያን ዳርቻ ትይዩ በተዘረጋው ምድረ በዳ ውስጥ በአርኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና።
ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን ነጠቁአቸው፥ ጌታ የሰጣቸውን እስራኤላውያን በርስት ምድራቸው እንዳደረጉት፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ተቀመጡ።
የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ ጌታ እንደ ማለባቸው የጦረኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።