ዘዳግም 19:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፤ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፤ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገዳዩ የሚኖርበት ከተማ መሪዎች ሰው በመላክ እነርሱም ነፍሰ ገዳዩን አስመጥተው የሟቹን ደም ለመበቀል መብት ላለው የቅርብ ዘመዱ አሳልፈው ይስጡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከተማው ሽማግሌዎች ይልካሉ፤ ከዚያም ይይዙታል። በባለደሙም እጅ አሳልፈው ይሰጡታል፤ ይሞታልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማው ሽማግሌዎች ይልካሉ፥ ከተማጠነበትም ከተማ ይነጥቁታል፥ እንዲሞትም በደም ተበቃዩ እጅ አሳልፈው ይሰጡታል። |
እነሆ ዘመዶቼ ሁሉ በአገልጋይህ ላይ ተነሥተው፥ ‘ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፥ ወራሽ እንኳ ብናጠፋ ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለን’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን በማጥፋት፥ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”