ዘዳግም 18:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአምላክህ በጌታ ፊት ነውር አልባ ሁን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ነውር አልባ ሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን ለእግዚአብሔር በፍጹም ታማኝ መሆን ይገባሃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን። |
ጌታም ሰይጣንን፦ “በውኑ አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም” አለው።
እኔ ግን አሁን ይህን አላገኘሁትም ወይም አሁን ፍጹም ለመሆን አልበቃሁም፤ ዳሩ ግን ክርስቶስ ኢየሱስ የራሱ አድርጎኛልና ይህን የራሴ ለማድረግ ወደ ፊት እሮጣለሁ።
“እንግዲህ አሁን ጌታን ፍሩ፥ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት አገልግሉት፤ አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብጽም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ ጌታንም አምልኩ።