ዘዳግም 18:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም በድግምት የሚጠነቁል፤ መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከልህ ከቶ አይገኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም በድግምት የሚጠነቍል፣ መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከልህ ከቶ አይገኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም ደግሞ መናፍስትን የሚጠራ ወይም ከመናፍስት ጋር የሚነጋገር፥ ወይም የሙታን መናፍስትን የሚስብ አይኑር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም፥ በወፍም የሚያሟርት በአንተ ዘንድ አይገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቁልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቍይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። |
ሰዎች፤ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?
“የሙታን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም በሚከተል፥ በሥራቸውም በሚያመነዝር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊራለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
ስለዚህ ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ መልኩን ለውጦ ከሁለት ሰዎች ጋር በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄደ። እርሱም፥ “እባክሽ፥ መናፍስትን ጠይቂልኝ፤ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ” አላት።