በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳም ልጆች የበሬውንና የበጉን አሥራት፥ ለአምላካቸውም ለጌታ የተቀደሰውን አሥራት አመጡ፥ ከምረውም አስቀመጡት።
ዘዳግም 14:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በየሦስት ዓመቱም መጨረሻ የዚያን ዓመት ሰብል አሥራት በሙሉ አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየሦስት ዓመቱ መጨረሻ የዚያን ዓመት ሰብል ዐሥራት በሙሉ አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ አከማች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ ላይ ከእርሻችሁ ሰብል ሁሉ ከዐሥር አንዱን እያወጣችሁ በከተሞቻችሁ አከማቹ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት የፍሬህን ዐሥራት ሁሉ አምጥተህ በከተማዎችህ ውስጥ ታኖረዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት የፍሬህን አሥራት ሁሉ አምጥተህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ታኖረዋለህ፤ |
በይሁዳም ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳም ልጆች የበሬውንና የበጉን አሥራት፥ ለአምላካቸውም ለጌታ የተቀደሰውን አሥራት አመጡ፥ ከምረውም አስቀመጡት።
“የእስራኤል ልጆች ሆይ! ይህን ወድዳችኋልና ወደ ቤቴል ኑና ኃጢአትን ሥሩ፤ ወደ ጌልገላ ኑና ኃጢአትን አብዙ፤ በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፥ በየሦስተኛውም ቀን አሥራታችሁን አምጡ፤