ዘዳግም 14:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጹሕ የሆነውን ማናቸውንም ክንፍ ያለውን ፍጡር ትበላላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጹሕ የሆነውን ማንኛውንም ክንፍ ያለውን ፍጡር ግን ብሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከእነርሱ መካከል በተለይ ንጹሓን የሆኑትን ትበላላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ንጹሓን የሆኑትን ወፎች ሁሉ ብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጹሕ የሆኑትን ወፎች ሁሉ ብሉ። |
“አንተ ግን ለጌታ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህና የሞተውን ሁሉ አትብላ፤ ከከተሞችህ በአንዲቱ ለሚኖር መጻተኛ እንዲበላ ልትሰጠው ትችላለህ፤ ወይም ለውጭ አገር ሰው ልትሸጠው ትችላለህ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።