ነገር ግን በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥም በሕይወት ከሚኖሩ ነፍሳት፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸውን ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።
ዘዳግም 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክንፍና ቅርፊትም የሌለውን ግን አትብሉ፤ ለእናንተ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ግን አትብሉ፤ ለእናንተ ርኩስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በውሃ ውስጥ የሚገኘው ክንፍና ቅርፊት የሌለው ፍጥረት ሁሉ አይበላም፤ እንደነዚህ ያሉት እንስሶች በእናንተ ዘንድ የረከሱ ሆነው መቈጠር አለባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም፤ ለእናንተ ርኩሳን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም፤ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። |
ነገር ግን በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥም በሕይወት ከሚኖሩ ነፍሳት፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸውን ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።
ማንም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም የረከሰን እንስሳ ወይም ምንም ዓይነት ርኩስ ሆኖ የተጠላን ማናቸውንም ርኩስ ነገር ነክቶ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።”