“በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።
ዘዳግም 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ማረፊያ ወደ ሆነውና ጌታ አምላካችሁ ወደ የሚሰጣችሁ ርስት ገና አልደረሳችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ማረፊያ ወደ ሆነውና አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ርስት ገና አልደረሳችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁና በሰላም ዕረፍት አድርጋችሁ ወደምትኖሩባት ርስት ገና አልገባችሁም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ማረፊያና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልደረሳችሁምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና። |
“በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።
ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፥ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ መደምሰስን፥ ይህንን አትርሳ።”
ይኸውም ጌታ እናንተን እንዳሳረፈ፥ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁሉ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።”
በእናንተ ቃላት ምክንያት ጌታ እኔን ተቆጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር ጌታ አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።
ጌታም ለሙሴ እንደ ተናገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደየነገዳቸው ድርሻ ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።