ዘዳግም 12:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፤ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ አንተ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፣ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፣ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፣ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክህ እግዚአብሔር በሚመርጥልህ ቦታ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ፥ እንዲሁም በከተሞችህ ከሚኖሩ ሌዋውያን ጋር እነዚህን ትበላለህ፤ እዚያም በድካምህ ያገኘኸውን መልካም ነገር ሁሉ ትደሰትበታለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አንተ፥ ወንድና ሴት ልጅህም፥ ወንድና ሴት አገልጋይህም፥ በሀገርህም ውስጥ ያለው መጻተኛ አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ብሉት፤ እጅህንም በምትዘረጋበት ነገር ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም፥ ባሪያዎችህና ገረዶችህም፥ በአገርህም ደጅ ያለው ሌዋዊ አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ብሉት፤ እጅህንም በምትዘረጋበት ነገር ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበልህ። |
እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ሀብትና ንብረት መስጠቱ፥ ከእርሷም ይበላና እድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ሥልጣን መስጠቱ ነው፥ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”
ምንጊዜም ጌታ እግዚአብሔርን ማክበር ትማር ዘንድ፥ የወይን ጠጅና የዘይትህን አሥራት፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት ስሙ እንዲጠራበት በሚመርጠው ስፍራ፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበላለህ።
ሕልቃና መሥዋዕት የሚሠዋበት ወቅት በደረሰ ጊዜ ሁሉ፥ ለሚስቱ ለጵኒና እንዲሁም ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችዋ ሁሉ ድርሻቸውን ይሰጣቸው ነበር።