እስራኤል በሰላም በእግዚአብሔር ክብር እንዲሄድ፥ እግዚአብሔር ረጃጅም ተራሮች ሁሉና ኮረብታዎች ዝቅእንዲሉ፥ ሸለቆዎች እንዲሞሉ፥ መሬትም እንዲስተካከል አዟልና።
እግዚአብሔርም ረጃጅሞች ተራሮች ሁሉ ዝቅ ይሉ ዘንድ፥ ጐድጓዳውም ሁሉ ይሞላ ዘንድ፥ ምድርም ይስተካከል ዘንድ፥ እስራኤልም በእግዚአብሔር ክብር በጥርጊያው ጐዳና ይሄድ ዘንድ አዘዘ።