Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ባሮክ 5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ኢየሩሳሌም ሆይ የኀዘንና የመከራ ልብስሽን አውልቂ፥ ለዘለዓለም ከእግዚአብሔር ክብር የሚወጣውን ውብት ልበሺ። 2 ከእግዚአብሔር የሚመጣውን የጽድቅ ካባ ደርቢ፤ የዘላለማዊውን የክብር አክሊል በራስሽ ላይ ድፊ። 3 እግዚአብሔር የብርሃንሽን ነጸብራቅ ከሰማይ በታች ላሉ ሁሉ ያሳያልና፤ 4 ስምሽ ከእግዚአብሔር ዘንድለዘለዓለም “ሰላም፥ ጽድቅና እግዚአብሔርን የመፍራት ክብር” ተብሎ ይጠራል። 5 ኢየሩሳሌም ሆይ ተነሺ! በከፍታ ላይ ቁሚ፤ ወደ ምሥራቅም ተመልከቺ፥ እግዚአብሔር ስላሰባቸው በመደሰት በቅዱሱ ቃል ከምሥራቅና ከምዕራብ የተሰበሰቡትን ልጆችሽን እዪ፤ 6 በጠላቶቻቸው ከአንቺ ሲወሰዱ በእግር ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እንደ ንጉሥ ዙፋን በክብር ወደ አንቺ ይመልሳቸል። 7 እስራኤል በሰላም በእግዚአብሔር ክብር እንዲሄድ፥ እግዚአብሔር ረጃጅም ተራሮች ሁሉና ኮረብታዎች ዝቅእንዲሉ፥ ሸለቆዎች እንዲሞሉ፥ መሬትም እንዲስተካከል አዟልና። 8 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጫካዎችና መልካም መዓዛ ያለው ዛፍ ሁሉ እስራኤልን በጥላቸው ጋረዱ። 9 እግዚአብሔር እስራኤልን በደስታ፥ በክብሩ ብርሃን፥ ከእርሱ በሚመጣ በምሕረቱና በጽድቁ ይመራቸዋልና። |