Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ባሮክ 5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! የኀ​ዘ​ን​ሽ​ንና የመ​ከ​ራ​ሽን ልብስ ከአ​ንቺ አው​ል​ቂው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያገ​ኘ​ሽ​ውን የክ​ብር ጌጥ​ሽ​ንም ልበሺ።

2 ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የጽ​ድቅ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ሽን ተጐ​ና​ጸፊ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ማ​ዊ​ውን አም​ላክ የክ​ብር ዘው​ድ​ሽ​ንም በራ​ስሽ ላይ ተቀ​ዳጂ።

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ በታች ላሉ ሁሉ ብር​ሃ​ን​ሽን ገል​ጧ​ልና።

4 ስም​ሽም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የጽ​ድቅ ሰላ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የመ​ፍ​ራት ክብር ተብሎ ይጠ​ራል።

5 ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ተነ​ሥ​ተሽ፥ በላ​ይ​ኛ​ውም ቦታ ቁሚ፤ ወደ ምሥ​ራ​ቅም ተመ​ል​ከቺ፤ ከም​ዕ​ራ​ብና ከም​ሥ​ራ​ቅም በቅ​ዱሱ ቃል ልጆ​ችሽ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ እዪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በማ​ሰብ ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

6 ከአ​ን​ቺም በእ​ግር ወጡ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወሰ​ዷ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ንጉሥ ዙፋን በክ​ብር ተሸ​ክ​መው ወደ አንቺ እን​ዲ​ያ​መ​ጧ​ቸው ያደ​ር​ጋል።

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ረጃ​ጅ​ሞች ተራ​ሮች ሁሉ ዝቅ ይሉ ዘንድ፥ ጐድ​ጓ​ዳ​ውም ሁሉ ይሞላ ዘንድ፥ ምድ​ርም ይስ​ተ​ካ​ከል ዘንድ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በጥ​ር​ጊ​ያው ጐዳና ይሄድ ዘንድ አዘዘ።

8 እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ዛፍ ሁሉ፥ በጎ መዓዛ ያለው ዕን​ጨ​ትም ሁሉ ይጋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ልና።

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን በደ​ስ​ታና፥ በክ​ብሩ ብር​ሃን፥ በም​ሕ​ረ​ቱና ከእ​ርሱ በሆ​ነች በጽ​ድ​ቁም ያመ​ጣ​ቸ​ዋ​ልና።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos