ሐዋርያት ሥራ 7:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶቻችንም ድንኳኗን ከተቀበሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር በኢያሱ መሪነት ያሳደዳቸውን የአሕዛብን አገር በወረሱ ጊዜ ይዘዋት ገቡ፤ እስከ ዳዊትም ዘመን ድረስ በምድሪቱ ተቀመጠች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከፊታቸው ያባረረላቸውን የአሕዛብን አገር በወረሱ ጊዜ አባቶቻችን ይህችን የተቀበሉአትን ድንኳን ከኢያሱ ጋር ወደዚያ አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ እዚያ ኖረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱና አባቶቻችንም በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ፊት አስወጥቶ ወደ ሰደዳቸው ወደ አሕዛብ ሀገር ከእነርሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። |
ልጆቹም ገብተው ምድሪቷን ወረሱ፤ የምድሪቱን ሰዎች ከነዓናውያንን በፊታቸው ደመሰስካቸው፥ የወደዱትን ነገር እንዲያደረጉባቸው ከነገሥታቶቻቸውና ከምድሪቱ ሕዝቦች ጋር በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
“ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፥ ከዓባሪም ተራራዎች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ነቦ ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት።
ስለዚህ ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ልከው፥ በኪሩቤል መካከል በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን የሠራዊት ጌታን የኪዳን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ከኪዳኑ ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።