Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 18:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ስለዚህም ሚካ የሠራቸውን ጣዖታት፥ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ አቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ስለዚህም ሚካ የሠራቸውን ጣዖታት፣ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ባለማቋረጥ አመለኳቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 በዚህም ዐይነት የሚካ ጣዖት እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በሴሎ እስከ ነበረበት ዘመን በዚያው ቈየ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሚካም ያደ​ረ​ገ​ውን የተ​ቀ​ረፀ ምስል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሴሎ ባለ​በት ዘመን ሁሉ አቆሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሚካም ያደረገውን የተቀረጸ ምስል የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ ባለበት ዘመን ሁሉ አቆሙ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 18:31
8 Referencias Cruzadas  

የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፥ በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ እነርሱም የምድሪቱ ገዢዎች ሆኑ።


ያም ሰው በየዓመቱ ለሠራዊት ጌታ ለመስገድና መሥዋዕት ለመሠዋት ከሚኖርበት ከተማ ወደ ሴሎ ይወጣ ነበር። በዚያም ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ የጌታ ካህናት ነበሩ።


ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኛ የመጣነው ከይሁዳ ቤተልሔም ርቆ ከሚገኘው ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር ነው፤ ከይሁዳ ቤተልሔም ነበርሁ፤ አሁን ወደ ጌታ ቤት እሄዳለሁ፤ ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ሰው አላገኘሁም።


ነገር ግን በቀድሞ ዘመን ስሜን ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደነበረው ስፍራዬ ሂዱ፥ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ምን እንዳደረግሁበት እዩ።


ስለዚህ ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ልከው፥ በኪሩቤል መካከል በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን የሠራዊት ጌታን የኪዳን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ከኪዳኑ ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።


አድፍጣችሁ ተጠባበቁ። የሴሎ ልጃገረዶች ለጭፈራ ወደዚያ በሚወጡበት ጊዜ፥ ከወይኑ አትክልት ቦታ ወጥታችሁ ከልጃገረዶቹ ለየራሳችሁ ሚስት ጥለፉ፤ ወደ ብንያምም ምድር ሂዱ።


ይሁን እንጂ ከቤቴል በስተ ሰሜንና ከቤቴል ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በስተ ምሥራቅ እንዲሁም ከለቦና በስተ ደቡብ ባለችው በሴሎ የጌታ በዓል በየዓመቱ ይከበራል።”


ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ተልትለው፥ በጌታ ቤት ለማቅረብ የእህል ቁርባንና ዕጣን በእጃቸው ይዘው፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios