አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።
ሐዋርያት ሥራ 7:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሴኬምም አፍልሰው አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር በገዛው መቃብር ቀበሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስከሬናቸውም ወደ ሴኬም ተወስዶ፣ አብርሃም ከዔሞር ልጆች ላይ በጥሬ ብር በገዛው መቃብር ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐጽማቸው ወደ ሴኬም ተወስዶ አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በገንዘቡ በገዛው መቃብር ተቀበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሴኬምም አፍልሰው አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በገንዘቡ በገዛው መቃብር ቀበሩዋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሴኬምም አፍልሰው አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር በገዛው መቃብር ቀበሩአቸው። |
አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።
ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት፥ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት፥ እርሷም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።
ሙሴም የዮሴፍን አጥንቶች ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ “በእርግጥ እግዚአብሔር ይጎበኛችኋል፥ አጥንቶቼንም ከዚህ ከእናንተ ጋር ውሰዱት” ብሎ የእስራኤልን ልጆች አምሎአቸው ነበርና።
የእስራኤልም ልጆች ከግብጽ ያወጡትን የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ ብር በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት፤ እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።