La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 28:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በብዙ ክብርም ደግሞ አከበሩን፤ በተነሣንም ጊዜ በመርከብ ላይ የሚያስፈልገንን ነገር አኖሩልን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኛንም በብዙ መንገድ አከበሩን፤ በመርከብም ለመሄድ በተዘጋጀን ጊዜ፣ የሚያስፈልገንን ሁሉ ጫኑልን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰዎቹ ብዙ ስጦታ አመጡልን፤ አክብሮታቸውንም ገለጡልን፤ በመርከብ ለመሄድ በተነሣንም ጊዜ የሚያስፈልገንን ሁሉ በመርከብ ላይ ጫኑልን።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እጅግ ታላቅ ክብ​ርም አከ​በ​ሩን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ለመ​ሄድ በተ​ነ​ሣን ጊዜ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንን ስንቅ ሰጡን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በብዙ ክብርም ደግሞ አከበሩን፥ በተነሣንም ጊዜ በመርከብ ላይ የሚያስፈልገንን ነገር አኖሩልን።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 28:10
15 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም አዛሄል በደማስቆ ከሚገኘው ምርጥ የምድር በረከት ሁሉ በአርባ ግመሎች ጭኖ ወደ ኤልሳዕ ሄደ፤ አዛሄልም ኤልሳዕን ባገኘው ጊዜ “ልጅህ ንጉሥ ቤንሀዳድ ከሕመሙ ይድን ወይም አይድን እንደሆነ እንድትነግረው እጠይቅህ ዘንድ ልኮኛል” አለው።


በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት እንዲያሳምር እንደዚህ ያለውን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥ የአባቶቻችን አምላክ ጌታ ይባረክ።


ኃጢአተኛ ሰው በፊቱ የተናቀ፥ ጌታን የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ቢጎዳም የማለውን የማይከዳ።


ከሦስት ወርም በኋላ በደሴቲቱ ከርሞ በነበረው በእስክንድርያው መርከብ ተነሣን፤ በእርሱም የዲዮስቆሮስ ዓላማ ነበረበት።


ይህም በሆነ ጊዜ የቀሩት ደግሞ በደሴቲቱ ደዌ የነበረባቸው እየመጡ ተፈወሱ፤


አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ያሟላላችኋል።


እንዲሁም ከእናንተም ሆነ ከሌሎች ክብርን አልፈለግንም፥