ሐዋርያት ሥራ 27:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፋሱም በርትቶ ሲያስጨንቀን በማንግሥቱ ከጭነቱ ወደ ባሕር ይጥሉ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማዕበሉም ክፉኛ ስላንገላታን፣ በማግስቱም ጭነቱን እያነሡ ወደ ባሕር ይጥሉ ጀመር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐውሎ ነፋሱ እየበረታብን ስለ ሄደ በማግስቱ በመርከቡ ላይ ከተጫኑት ዕቃዎች እያንዳንዱን ወደ ባሕር መጣል ጀመሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማግሥቱም ማዕበል ጸናብን፤ ከጭነቱም ወደ ባሕር ጣልን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፋሱም በርትቶ ሲያስጨንቀን በማንግሥቱ ከጭነቱ ወደ ባሕር ይጥሉ ነበር፥ |
መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱ እንዲቀልልላቸውም መርከቢቱ ውስጥ የነበሩትን ዕቃዎች ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ታችኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር።
እንግዲህ እነደዚህ ዓይነት ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ማንኛውንም ሸክምና የተጣበቅንበትን ኅጢአት ሁሉ አራግፈን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።