ሐዋርያት ሥራ 25:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንግዲህ በዚህ ሰው ክፋት ቢሆን ከእናንተ ዘንድ ያሉት ባለ ሥልጣኖች ከእኔ ጋር ወርደው ይክሰሱት፤” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ከባለሥልጣኖቻችሁ መካከል አንዳንዶች ከእኔ ጋራ ይምጡና ሰውየው ጥፋት ካለበት ክሱን በዚያው ያቅርቡ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለሥልጣኖቻችሁ ከእኔ ጋር ወደ ቂሳርያ ይሂዱ፤ ጳውሎስ ያደረገው በደል ካለ እዚያ ይክሰሱት” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድንም፥ “ከመካከላችሁ የሚችሉ ካሉ ከከሰሳችሁት ከዚያ ሰው ጋር እንዲከራከሩ ከእኔ ጋር ይውረዱ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ በዚህ ሰው ክፋት ቢሆን ከእናንተ ዘንድ ያሉት ባለ ስልጣኖች ከእኔ ጋር ወርደው ይክሰሱት አላቸው። |
በዚህም ሰው አይሁድ ሤራ እንደሚያደርጉበት ባመለከቱኝ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ አንተ ላኩት፤ ከሳሾቹንም ደግሞ በፊትህ እንዳይከሱት ዘንድ አዘዝኋቸው።
እኔም ‘ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ፥ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም፤’ ብዬ መለስሁላቸው።
በእነርሱም ዘንድ ከስምንት ወይም ከዐሥር የማይበልጥ ቀን ተቀምጦ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በነገውም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ያመጡት ዘንድ አዘዘ።