Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 18:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ጳውሎስም አፉን ሊከፍት ባሰበ ጊዜ፥ ጋልዮስ አይሁድን “አይሁድ ሆይ! ዐመፅ ወይም ክፉ በደል በሆነ እንድታገሣችሁ በተገባኝ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ጳውሎስ ሊናገር ገና አፉን ሲከፍት፣ ጋልዮስ አይሁድን እንዲህ አላቸው፤ “የአይሁድ ሰዎች ሆይ፤ ያቀረባችሁት ጕዳይ ስለ ዐመፅ ወይም ስለ ከባድ ወንጀል ቢሆን ኖሮ ላደምጣችሁ በተገባኝ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጳውሎስ መልስ ለመስጠት ተዘጋጅቶ ሳለ ጋልዮስ አይሁድን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የአይሁድ ወገኖች! በደል ወይም ከባድ ወንጀል ተፈጽሞባችሁ ቢሆን ኖሮ ክሳችሁን በትዕግሥት በሰማሁ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ጳው​ሎ​ስም ይመ​ል​ስ​ላ​ቸው ዘንድ አፉን ሊከ​ፍት ወድዶ ሳለ አገረ ገዢው ጋል​ዮስ መልሶ አይ​ሁ​ድን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ አይ​ሁድ ሆይ፥ የበ​ደ​ላ​ችሁ በደል ቢኖር፥ ወይም ሌላ በደል ቢኖ​ር​በት አቤ​ቱ​ታ​ች​ሁን በሰ​ማ​ሁና ባከ​ራ​ከ​ር​ኋ​ችሁ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ጳውሎስም አፉን ሊከፍት ባሰበ ጊዜ፥ ጋልዮስ አይሁድን፦ አይሁድ ሆይ፥ ዓመፅ ወይም ክፉ በደል በሆነ እንድታገሣችሁ በተገባኝ፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 18:14
17 Referencias Cruzadas  

አፉንም ከፍቶ እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፤


ኢየሱስም መልሶ፥ “የማታምን ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጁን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው።


“አንተ ተንኰል ሁሉ ክፋትም ሁሉ የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን?


በበረሃም አርባ ዓመት ያህል መገባቸው።


ጳውሎስ ግን “እኔስ አይሁዳዊ በኪልቅያ ያለው የጠርሴስ ሰው ሆኜ ስመ ጥር በሆነ ከተማ የምኖር ነኝ፤ ለሕዝቡ እናገር ዘንድ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ፤” አለ።


እንግዲህ በድዬ ወይም ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ እንደሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ የሚከሱኝ ክስ ከንቱ እንደሆነ ግን ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠኝ ዘንድ ማንም አይችልም፤ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ፤” አለ።


ስለ እርሱም ወደ ጌታዬ የምጽፈው እርግጥ ነገር የለኝም፤ ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈውን ነገር አገኝ ዘንድ በፊታችሁ ይልቁንም ንጉሥ አግሪጳ ሆይ!በፊትህ አመጣሁት፤


ገዢዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ፤


ሞኝነቴን በጥቂቱ ብትታገሡኝ በወደድኩ ነበር፤ ስለሆነም በእርግጥ ታገሡኝ።


ምክንያቱም አንዱ መጥቶ እኛ ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ሆኖ ብታገኙት፥ በመልካምነታችሁ ትታገሡታላችሁ።


እርሱ ራሱም ደግሞ ድካምን ስለሚለብስ፥ ላልተማሩትና ለሚሳሳቱት ሊራራላቸው ይችላል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos