Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 25:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በእነርሱም ዘንድ ከስምንት ወይም ከዐሥር የማይበልጥ ቀን ተቀምጦ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በነገውም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ያመጡት ዘንድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከእነርሱም ጋራ ስምንት ወይም ዐሥር ቀን ያህል ከሰነበተ በኋላ፣ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በማግስቱም ፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ፊስጦስ ከስምንት ወይም ከዐሥር ቀኖች ያልበለጠ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ካሳለፈ በኋላ ወደ ቂሳርያ ሄደ፤ እዚያ በደረሰ ጊዜ በማግስቱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠና ጳውሎስን እንዲያቀርቡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስም​ንት ወይም ዐሥር ቀን በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ነ​በተ በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ሄደ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም በፍ​ርድ ወን​በር ተቀ​ምጦ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በእነርሱም ዘንድ ከስምንት ወይም ከአስር የማይበልጥ ቀን ተቀምጦ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በነገውም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ያመጡት ዘንድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 25:6
11 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም በዚህ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ሳልዘገይ በማግሥቱ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ ያንን ሰው ያመጡት ዘንድ አዘዝሁ።


ጳውሎስ ግን “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሣር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም።


እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ፥ ሚስቱ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ ጻድቅ ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።


እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ፤ እናንተን የሚያስጨንቋችሁ ሀብታሞች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጐትቷችሁስ እነርሱ አይደሉምን?


መልካም ሆነ ወይም ክፉ፥ በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን ለመቀበል፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።


ጲላጦስም ይህን ነገር ሰምቶ ኢየሱስን ወደ ውጭ አወጣው፤ በዕብራይስጥም ገበታ በተባለው “ጠፍጣፋ ድንጋይ” በሚሉት ስፍራ በፍርድ ወንበር ተቀመጠ።


ፊልጶስ ግን በአዛጦን ተገኘ፤ ወደ ቂሣርያም እስኪመጣ ድረስ እየዞረ በከተማዎች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።


ፊስጦስም ወደ አውራጃው ገብቶ ከሦስት ቀን በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።


ፊስጦስ ግን ጳውሎስ በቂሳርያ እንዲጠበቅ እርሱም ራሱ ወደዚያ ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ እንዳለው መለሰላቸው፤


“እንግዲህ በዚህ ሰው ክፋት ቢሆን ከእናንተ ዘንድ ያሉት ባለ ሥልጣኖች ከእኔ ጋር ወርደው ይክሰሱት፤” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios