ሐዋርያት ሥራ 25:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጳውሎስ ግን “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሣር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “አሁንም ቢሆን ፍትሕ ማግኘት በምችልበት፣ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ምንም በደል አልፈጸምሁም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጳውሎስ ግን እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “እነሆ! እኔ ልፋረድበት በሚገባኝ በሮም ንጉሠ ነገሥት የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ፤ አንተም በደንብ እንደምታውቀው በአይሁድ ላይ ያደረግኹት ምንም በደል የለም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጳውሎስም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀርባለሁ፤ ፍርዴም በዚያ ሊታይልኝ ይገባል፤ በአይሁድም ላይ የበደልሁት በደል እንደሌለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጳውሎስ ግን፦ “እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልኩም። |
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ፥ ሚስቱ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ ጻድቅ ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።
በእነርሱም ዘንድ ከስምንት ወይም ከዐሥር የማይበልጥ ቀን ተቀምጦ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በነገውም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ያመጡት ዘንድ አዘዘ።
የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል፤ በተንኮል አንመላለስም ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናቀርባለን።