ሐዋርያት ሥራ 2:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተሰበረ፤ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት “ወንድሞች ሆይ! ምን እናድርግ?” አሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ልባቸው እጅግ ተነካ፤ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም ሐዋርያት፣ “ወንድሞች ሆይ፤ ታዲያ ምን እናድርግ?” አሏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ልባቸው በሐዘን ተነክቶ ጴጥሮስንና ሌሎቹን ሐዋርያት፥ “ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን እናድርግ?” አሉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተከፈተ፤ ጴጥሮስንና ወንድሞቹ ሐዋርያትንም፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምን እናድርግ?” አሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተነካ፥ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት፦ “ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ?” አሉአቸው። |
በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
ወታደሮችም እንዲሁ፦ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ “ማንንም በግፍ ወይም በሐሰት ክስ አትበዝብዙ፤ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ፤” አላቸው።
“ወንድሞች ሆይ! ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤