ሐዋርያት ሥራ 12:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቃል ግን እያደገና እየሰፋ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ቃል ግን ዘወትር እያደገና እየተስፋፋ ይሄድ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቃል ከፍ አለ፤ በዛም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር። |
ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ እንድታበቅልና እንድታፈራም እንደሚያደርጋት፥ ዘርንም ለሚዘራ፥ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥
የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።
ይህም ወንጌል ወደ እናንተ ደርሶአል፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ በእውነት ከሰማችሁበትና ካወቃችሁበት ቀን ጀምሮ፥ በእናንተ መካከል እንደ ሆነው እንዲሁ በመላው ዓለም ፍሬ ያፈራል፤ ያድጋልም።